ስሞች | ማንኛውም ነገር | መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ | ብሉይ ኪዳን & ሐዲስ ኪዳን | ትምህርተ ሃይማኖት |
---|---|---|---|---|
አሮን
ይህ ሰው ሙሴን እስራኤላውያንን ከግብፅ እንዲያወጣ ረድቶታል::
|
2018
የሁለቱ ቅዱስ ሲኖዶስ እርቅ በፈረንጆች አቆጣጠር በምን አ.መ. ተፈፀመ?
|
ማቴዎስ 22:39
“ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።”
|
ማቴ 2፥13
የእመቤታችን የስደት ጊዜ 3 ዓመት ከ6 ወር የተገለፀበት የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው?
|
Dogma
የግርክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ መሠረተ እምነት፣ የማይለወጥ፣ የማይቀየር፣ የማይሻሻል፣ የማያረጅ ማለት ነው
|
ነገድ ቢንያም
ይህ ነገድ ለእስራኤል የመጀመሪያውን ንጉሥ ሰጠው::
|
ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ
እኝህ አባት ማን ይባላሉ
|
የሉቃስ ወንጌል 1:28
“መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤
አንቺ ከሴቶችመካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።”
|
ዲያብሎስ
ኢየሱስም፡— ሰው በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ
በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል
ብሎመለሰለት, ለማን ነው ይሄ መልስ የተሰጠው
|
የምሥጢረ ቁርባን አገልግሎት /ጥቅም/
በዚህ አማካኝነት የዘለዓለም ሕይወት እናገኛለን
|
ቅድስ ጴጥሮስ
እንድርያስ Matthew 4:18
ኢየሱስን እንዲከተሉ የተጠሩ የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት እነዚህ ናቸው::
|
ይህን ሲለን ከመዘንጋት አልጋ በንቃት፤ ከክፋት መኝታ አልጋ በቅንነትና በተመስጦ ከአምላካችሁ ጋር በጸሎትተገኛኙ ማለቱ ነው፡፡ አንድም ክብሩንና የአምልኮቱ ዜና ሲነገር መቀመጥ አይቻልም ማለቱ ነው፡፡
የተቀመጣችሁ ተነሱ/ሁለተኛ
ትርጓሜውን ስጥ
|
1ኛ ሳሙኤል 16:7
“ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል፡ አለው”
|
የሐዋርያት ሥራ
የቅዱስ ጳውሎስን የሕይወት ታሪክ መዝግቦ የያዘው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው??
|
ሃያ ሁለቱን ፍጥረታት በሦስት መንገድ ፈጠረ።
በአርምሞ /በዝምታ/ (7 ፍጥረት) 2. በነቢብ /በመናገር/ (14 ፍጥረት) 3. በገቢር /በመሥራት/ (1 ፍጥረት) ሰውን ፈጠረ።
ሃያ ሁለቱን ፍጥረታት በስንት መንገድ ፈጠረ፣ዘርዝር
|